ምእራፍ - 2

ዱላ ይወዳል አሉ


አንድ ሰው ነበረ ከጥንት የሚያቀን

አገራችን ገብቶ ሲያደርግ ያሻውን

መንግስት እንኳ ሳይቀር እሱ እንደፈለገ ሲቀይርልን

መሬታችን ሳይቀር ቆርሰን እንድንሰጥ ግዳጅ ሲያስገባን

ምንም ሳንቃወም ሁሉን እሺ ያልነው ኸረ ለምን ይሆን ?


በሕግ አንጠይቀው ወይ ተው አንለው

ይህን ሁሉ ሐጢያት ሲሰራ እያየነው


የዋህ ስለሆንን እንደ ሞኝ ቆጥሮን

ይኸው ከናካቴው ወኪል አስመጥቶ ገባር አደረገን


ጥንት እንደሚባለው የአበው ተረት

ዶሮን በመጫኛ ጠልፈው ቢጥሎት

የስዎች ሞኝነት እንዴት ይገርማት


እርዳታ እስጣለሁ ብሎ ሲመጣደቅ ዝንተ አመታት

ባይናችን አያየን ሕዝብ እየተራበ እንዲሁም ሲሞት

ገንዘቡ የት ገባ ብሎ እንደማጣራት ከስር መስረት

ቢያቆም ይሻለዋል በኛ ላይ መቀለድ ይሄ ግታንግት


ለሱ ሰላም ብለን እኛ ልንሰቃይ

ምን አይነት ሆዳም ነው አዙሮ የማያይ

ግፍ መስራት ያስቀጣል በየዋህ ሕዝብ ላይ


ባንድ ኢትዮጵያ ሰም ጠንክሮ ከስራ ሕዝቡ ከበረታ

መኖር እንችላለን ከዚህ የተሻለ ያለሱ እርዳታ


ታሪኩን ስናነብ ስንመረምር

ደስ ይለዋል አሉ ዱላና በትር


አጉል ጠባይ ሆኖ የማያደርገውን አደርጋለሁ ይላል

ጥሩ ሰው ነው ብለህ አምነህ ስትጠጋው ወዲው ይከዳሀል

እንዲሁ ዝም ብሎ ከምድር ተንስቶ ሰው መናቅ ያበዛል

ዱላዋን ካየ ግን ትንሽ እንኳ ሳይቆይ ምንልታዘዝ ይላል


ከዚህ በኍላ ነው እርዳታ መለገስ

የተመሰረተ በጋራ ትብብር በኩልነት መንፈስ


ቃልም እንገባለን እሱ ካልሸወደን እኛ ላንሸውደው

እንደዚያ ሲሆን ነው አገራችን ሲኖር ሰላም የሚያገኘው

በዚህ ካልተስማማ ለያዘው በሽታ ፈውስ እንዲሆነው

ዱላው እንኳ ቢቀር ሳማ ሜዳ ወስዶ ማንከባለል ነው


Author - Amigo ZorometaChapter-3 ..... Next
© 2016 Ethiocartoons.net